~~~~~~የጥያቄ ቀን~~~~~~ (የንባብ ጥቅሶች ማቴ 21:23-27 ፣ ማር 11:7-33 ፣ ሉቃ 20:1-8 ) የሠሙነ ህማማት ሠሉስ(ማክሰኞ) " #የጥያቄቀን " በመባል ይታወቃል ምክንያቱም ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጾሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበረ። ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኃለው የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም? ይለናል ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህርም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸው ሁሉ በራሱ ስልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ ። ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው። በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ #የትምህርትቀን በመባልም ይታወቃል። ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምረን ነው። ማቴ21፣28 እና ማቴ25፣46 ማር 12፣2 እና ማር13፣37 ሉቃ20፣9 እና ሉቅ21፣38 #Himamat እምበለ ደዌ ወሕማም፤ እምበለ ጻማ ወድካም አመ ከመ ዮመ ያብጸሐነ፤ ያብጸሐክሙ እግዚአብሔር በሰላም። (at Debreselam Medhanealem EOTC Minnesota) https://www.instagram.com/p/BwmdzrfAh4K/?utm_source=ig_tumblr_share&igshid=1azggh3s8yeb













