#senselet #TheHabeshaWeb https://www.instagram.com/p/B18UkKYnD8F/?igshid=16ojrb0bdeuav

seen from Singapore
seen from United States

seen from Russia
seen from Kazakhstan

seen from Malaysia
seen from Switzerland
seen from Poland

seen from Malaysia
seen from United States
seen from Germany

seen from Malaysia
seen from United States
seen from Germany
seen from Saudi Arabia

seen from Germany

seen from Germany
seen from China

seen from Libya

seen from United Kingdom
seen from Italy
#senselet #TheHabeshaWeb https://www.instagram.com/p/B18UkKYnD8F/?igshid=16ojrb0bdeuav
በሚዲያ የተሰራጨው የአርቲስት #ትዕግስትን ጉዳይ በተመለከተ እውነታው ይህ ነው! በ #Senselet ድራማ ተዋናይዋነት የምትታወቀዋን አርቲስት #ትዕግስት ስታመነዝር ተያዘች ተብሎ በሚዲያ ቪዲዮዋ ተለቅቆ ብዙዎች በLike, Share, Comment ድንጋይ ሲወረውሩባት ቆይተዋል፣ አሁንም እየወረወሩባት ይገኛሉ፣ ፈጣሪ ይቅር ይበላቸውና። ነገር ግን እንደተባለው የልጅቷ ድርጊቱን መፈጸም አለመፈጸም ጉዳይ አሁንም ድረስ የተረጋገጠ ሆኖ አይታይም፣ ቀደም ሲል አንዳንዶች ትዕግስትን አነጋግረውና ጥፋተኛ እንደሆነች ታምኖ ጉዳዩ በእርቅና በመስማማት ላይ እንደሆነ የገለጹ ሰዎች ነበሩ፣ በቅርቡ ደግሞ ትዕግስት እራሷ በሰይፉ ፋንታሁን ስለጉዳይ ተጠይቃ ነገሩ ከእውነት የራቀ እንደሆነና የቀረጸቻት ሴትም ባለመረዳት እንደሆነ ተናግራለች። ለማንኛውም አመንዝራለች የተባለው እውነት ቢሆን እንኳን ትምህርት ወስዶ ማለፍና መልካሙን ከመመኘት፣ እንዲሁም ከመጸለይ ባሻገር በሚዲያ እየተደረገ ያለው መሳለቅና መፍረድ ተገቢ አይደለም። ለመሆኑ ከእያንዳንዳችሁ ያላመነዘረ አለ? ልብ በሉ፣ «ሐጢያት ያልሰራ አለ ወይ» ብቻ አይደለም ያልኩት፣ ከእያንዳንዳችሁ «ያላመነዘረ» አለ ወይ? አላስተዋልንም እንጂ እያንዳንዳችንም ከሌሎች ሐጢያታችን በተጨመሪ አመንዝረናል። እንዴት ካላችሁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል 5፡27-28 ያለውን ልብ ብላችሁ አንብቡ። ቃሉም እንዲህ ይላል፡ የማቴዎስ ወንጌል 5 27 አታመንዝር እንደ ተባለ ሰምታችኋል። 28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል። እና፣ በዚህ መሰረት ከእናንተ መሃል በአካልም ሆነ በቲቪ/ስልካችሁ ላይ ያያችሁትን ሴትም ሆነ ወንድ በልቡ ተመኝቶ የማያውቅ ሰው አለ? የለም! ስለዚህ ሁላችንም አመንዝሮች ነን ማለት ነው! እውነታው ይህ ነው። ታዲያ ከራሳችን ውድቀት በንሰሃ ተነስተንና በርትተን የወደቀውን ለማንሳት መጣር ሲገባን ለምንድነው በወደቀው ላይ ድንጋይ የምንወረውረው ወይም የምንፈርደው? አርቲስቷ ጥፋተኛ ሆነችም አልሆነችም፣ እኛ ግን በምን ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው? ይህ ጉዳይ ከሁሉም በላይ በጣም ሊያሳስበን ይገባል፣ ምክንያቱም የምንሞትበትን አናውቅም፣ ንሰሃ ሳንገባ ከሞትን ደግሞ የሚገጥመን የዘላለም እሳት(ገሃነም) እንጂ የዘላለም ህይወት አይደለም። ልብ በሉ፡- የማይቀርልን፣ ቀኑም የማይታወቀው ሞት ወስዶን ለፍርድ ቀን ስንቀርብ ያን ጊዜ ለእያንዳንዱ ጥፋታችን እንጠየቅባቸዋለን፡፡ አንዳንዶቻችን ከምግብ ስለምንጾም፣ ወይም በቤተ እምነት ስለምንመላለስ፣ እና በህይወት ሳለን ያደረግናቸው ጥሩ ነገሮች ስለአሉ፣ እነዚህን ወይም አንዳንድ ትዕዛዛትን ባንጠብቅ የሚፈረድብን አይመስለንም። ግን በጣም ተሳስተናል። ምክንያቱም ያላስተዋልነው ነገር፣ ለምሳሌ፦ አንድ ሰው በእድሜ ዘመኑ ጥሩ ነገር ሲያደርግ ቢኖርም እንኳን፣ አንድ ቀን ግን ከሰው ጋር ተጣልቶና የተጣላውን ሰው ሳያስብም ቢሆን ገድሎት ወይም ከፍተኛ በደል አድርሶበት ዳኛ ፊት ቢቀርብ፣ ሰውዬው ዳኛውን፣ «ክቡር ዳኛ፣ እስከዛሬ እኮ ብዙ ጥሩ ነገሮችን ሰርቻለሁ፣ ዛሬ ብቻ ነው በሰው ላይ በደል የፈጸምኩት» ብሎ በይቅርታ እንዲፈቱት ቢጠይቅ፣ ባጠፋው ጥፋት ተፈርዶበት ይታሰራል እንጂ እስከዛሬ ያደረጋቸው ጥሩ ነገሮች ለጥፋቱ ዋስትና ሊሆኑለት አይችሉም። ያ ሰው ሊፈታ የሚችለው ለጥፋቱ ዋስትና ወይም ዋጋ ከተከፈለለት ብቻ ነው። የafterlife ፍርድ ቀንም እንደዛው ነው! ስለምንጾም፣ ወይም ደግሞ በቤተ እምነት ስለምንመላለስ፣ እና ያደርግናቸው ብዙ ጥሩ ነገሮች ቢኖሩም፣ የሚፈረድብን በጥፋታችን ወይም በመሳደባችን፣ ዘረኞችና ትዕቢተኞች በመሆናችን፣ እንዲሁም በሌሎችም ጥፋቶቻችን ይፈረድብናል እንጂ እስከዛሬ ያደረግናቸው ነገሮች ለጥፋታችን ዋስትና ሊሆኑልን አይችሉም። ስለዚህ፣ ለጥፋታችን የግድ ዋጋው ካልተከፈለልን በቀር ገነት ልንገባ አንችልም ማለት ነው! [ቀጣዩን ንባብ በኮመንት ላይ.. https://www.instagram.com/p/B0IUZFmBaBt/?igshid=2oe0n6c425gi