ዛሬ መጋቢት 24 የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት መታሰቢያ እለት ነው። የመጋቢት 24 ልዩ የሚያደርገው የፅንሰታቸው እለት ስለሆነ ነው። ተክለሃይማኖት ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ማለትም “አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው” በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡ ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር፡፡ ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ሀይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል፡፡ ካገለገሉባቸው ቦታዎች አማራ ሳይንት ወሎ፣ ትግራይ(ደብረዳሞ) ፣ ወላይታ ፣ ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም፣ እና ደብረሊባኖስ ይገኙባቸዋል። ከ1267-1289 ዓ.ም ባለው ጊዜ በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት 8 ጦሮችን (ሁለቱን በፊት፣ ሁለቱን በኋላ፣ ሁለቱን በቀኝ፣ ሁለቱን ደግሞ በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትና ቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች፡፡ ቅዱስ አባታችን በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቁመት በተጋድሎ ብዛት አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለደቀ መዛሙርቶቻቸው አስቀድመው ‹‹ልጆቼ ሆይ! ሁሉም የመነኮሰ መንግሥተ ሰማይ ይገባል ማለት አይደለም ዓለምን በሚገባ የናቀ ብቻ ይገባል እንጂ፡፡ መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ጽድቁን ብቻ ፈልጉ፤ ጾምና ጸሎትን አዘውትሩ፤ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ ትእዛዛቱንም አጥብቃችሁ ጠብቁ›› እያሉ ከመከሯቸው በኋላ ስለራሳቸውም ሲናገሩ «ለዓለም ጨው ለራሴ አልጫ ሆንኩ፤ ለዓለም ብርሃን ለራሴ ጨለማ ሆንኩ፣ ከእውነተኛው ዳኛ ከጌታዬ ፊት ስቆም ምን እመልሳለሁ?» እያሉ በፍጹም ትህትና እና በልዩ መንፈሳዊ ተመስጦ ይጸልዩ ነበርና አሁንም አባታችን የከበረች ቅድስት ነፍሳቸው ከሥጋቸው ሳትለይና ይህን ዓለም ከሥጋ ከመለየታቸው በፊት የሚከተለውን የሃይማኖት ኑዛዜ አውርሰውናል፡- የጻድቁ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት በረከታቸው፣ ቃልኪዳናቸው፣ አማላጅነታቸው በሁላችን ላይ ለዘለዓለሙ ፀንቶ ይደር ...... አሜን። ወስብሓት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር አሜን ምንጭ (ከመልአከሰላም አባ ገብረሚካኤል fb ገፅ ተቀንጭቦ የተወሰደ) #EthiopianOrthodoxTewahdoChurch followers celebrate the blessed life of #AbuneTekleHaimanot #TheDebreLibanos #DebreLibanos #አቡነተክለሃይማኖት #ዘደብረሊባኖስ #TheOrthodoxWay #LiveOrthodoxy https://www.instagram.com/p/BvvY0C0Aqvu/?utm_source=ig_tumblr_share&igshid=mqzo21zzfnc2








