maya angelou

seen from Germany

seen from Lithuania

seen from Malaysia
seen from China

seen from South Africa

seen from Malaysia

seen from Malaysia
seen from United States
seen from United States

seen from United States

seen from Ireland
seen from China

seen from United States

seen from Japan
seen from United States
seen from United States

seen from United States
seen from United Kingdom

seen from Lithuania
seen from United States
maya angelou
Henock Sitotaw
NUREDIN ISA
Dereje Belayneh "Belit Jember"-1994E.C
አትቀስቅሱን
ከሰው በፊት ባነን፣ ነቅተናል የሚሉ ለዚህ ዘመን ትውልድ፣ ደውል ነን የሚሉ የተኛን ካልተኛ፣ መለየት ያልቻሉ በዚህች በኛ ቀዬ፣ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ከዓለም ሁካታ ፣ ማረፍ ለፈለገ ወይ አውቆ ለተኛ፣ ጆሮ ለነፈገ፤ ቀድሟቸው ለነቃ፣ ፈጥኖ ለተነሣ ምን ያደርግለታል? ለነቃ ቅስቀሣ?! እባካችሁ ተዉን፣ አትረብሹን በቃ መጀመሪያ ለዩ፣ የነቃን ካልነቃ! በቃ! ____ ዳኜ አሰፋ (የውብዳር ልጅ)
ኢትዮጲያዊ ነኝ!
( Bewketu Seyoum) ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣ እንደአክሱም ድንጋይ እንደሮሃ አለት፣ የጊዜ ሞገድ ያላደቀቀኝ፣ የመከራ ዶፍ ያልነቀነቀኝ፣ ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ፣ በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ከዋርካ ባጥር ከዕምቧይ ተልቄ፣ ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ፣ ከምድረበዳ ጅረት አፍልቄ፣ ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ልክ እንደቻይናው የትም ሳልረባ፣ እንደእንግሊዙ ሳልሰራ ደባ፣ እንደአሜሪካው በቁም ሳልሰባ፣ በመጠን ኑሬ አፈር 'ምገባ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ! ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ፣ ራስምታቴን በዳማከሴ፣ ነቅዬ 'ምጥል፣ አገር በነገር የማብጠለጥል፣ ነገር በነገር የማብጠለጥል፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ! እንደመሃረብ ቤቴን በኪሴ፣ እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ፣ ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ፣ በዘብ በኬላ የማልገታ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ!
“የ'ኛ እናት”
የ'ኛ እናት ነበረች... ከፋሽን ጫማ ይልቅ ባዶ እግሯን የምትደምቅ እሾህና አጋም ምንሜና ጋሬጣ ኑሮን ለማሸነፍ ይህን ሁሉ ተጋፍጣ አንድ ኪሎ እንጨት እልፍ ኪሎ ሜትር ጀርባዋ ላይ ጭና ያውም በባዶ እግር በለቀመችው እንጨት ምሽቱን አድማቂ ለቤቷ ምሰሶ የትዳሯ ሙቀት ብርሃን ፈንጣቂ የ'ኛ እናት ነበረች ለእምነቷ ኑራ ህይወት የሰጠች ከእሾህ ከጋሬጣ ጫማዋን የፈራች፤
ላንዲት መስቲካ ሻጭ ህጻን
በደብተርሽ ምትክ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ ካልፎሂያጅ እግር ስር፤ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ ጋሼ ግዙኝ ስትይ፤ ኣንጋጠሽ ወደ ላይ ለጉድ ተጎልቸ፤ ምታረጊውን ሳይ ራሴስ ይታመም፤ ምላሴን ምን ነካው ግራዋ ይመስል፤ መረረኝ ማስቲካው:: ኣፈር ጠጠር ለብሶ ፤በዶዘር ተድጦ መስኩ ከነጎርፉ ሰማይ ከነዶፉ ለጌቶች ተሽጦ ኣተር ነው እያሉ፤ ኣፈር ዘግኖ መፍጨት ገነት ነው እያሉ፤ መስክ ላይ መፈንጨት ጠበል ነው እያሉ፤ ተጎርፉ መራጨት ይህንን ማን ሰጦሽ ገና በልጅነት፤ ልጅነት ኣምልጦሽ፡፡ በምቢልታ በዋሽንት፤ በከበሮ ታጥሮ በክራር ተማግሮ በቆመ ከተማ እምባሽ ቅኝት የለው ፤ለሰው ኣይሰማ፡ ጠዋት የፎከረ ፤ቀትር ላይ ሲረታ ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ ፤ትናንት የበረታ ኑሮን ያህል ሸክም፤ ያላንቀልባ ሲያዝል፡፡ ምን ጸጋ ለብሶ ነው፤ ትከሻሽ የማይዝል፡፡