ሰዓሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን/2/ ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ....ከዋክብት ከዋክብት ለቤተክርስቲያን.... ከዋክብት
በምድረ ሊቢያ ተጣራ ኢየሱስ በተዋሕዶ ልጆች ስሙ እንዲቀደስ ኢየሱስ አምላክ እያሉ በጽናት መንግስተ ሰማይን ሕጻናት ተሻሟት
ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ....ከዋክብት ከዋክብት ለቤተክርስቲያን.... ከዋክብት
በመከራ ግዜ ሚዛን ላይ ወጥታችሁ በክርስቶስ ጸጋ እንደ እንቁ አበራችሁ እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰይፍን ሳትፈሩ እግዚያብሔር ይመስገን በቃችኹ ለክርብሩ
ሰዓሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን/2/ ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ....ከዋክብት ከዋክብት ለቤተክርስቲያን.... ከዋክብት
እዩ ሲያንገላቱት ሲያዳፉት ጨክነው ምንም አልቀመሰ ወንድሜ ጾሙን ነው ግን እንደ ሰርገኛ በደስታ ይጓዛል በሰይፍ ፊት ለወንጌሉ ታምኗል መከራውን ንቆ ለወንጌል ታምኗል
ሰዓሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን/2/ ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ....ከዋክብት ከዋክብት ለቤተክርስቲያን.... ከዋክብት
ግርፋት ወይስ መታረዱን ቢሆን ከክርስቶስ ፍቅር እኛን አይለየን ያመለክነው አምላክ እውነት ስለሆነ ለክብር ተፋጠኑ ልባቸው ጨከነ
ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ....ከዋክብት ከዋክብት ለቤተክርስቲያን.... ከዋክብት
የዋልዮሽ ታስረው እንደበግ ሲነዱ ይመስሉ ነበር ለሰርግ የሚሔዱ በጉድጓድ ተከተው ለቀናት ቢራቡ በውሀ ጥም ዝለው አልተነዋወጹም
ሰዓሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን/2/ ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ....ከዋክብት ከዋክብት ለቤተክርስቲያን.... ከዋክብት
ገዳዮች ድል ሆኑ ሙታን ሆኖ እነሱ የተዋሕዶ ልጆች በድል ገሰገሱ በደማቸው ጸዳል ዓለምን ቀየሩ የኢትዮጵያ ከዋክብት በሊቢያ አበሩ የኢትዮጵያ ከዋክብት በዓለም አበሩ
ከዋክብት ለቤተክርስቲያን ....ከዋክብት ከዋክብት ለቤተክርስቲያን.... ከዋክብት
https://www.youtube.com/watch?v=8gbvVYyrRjg&sns=fb