''መላው የአፍሪካውያን ሀገራት ከቅኝ ግዢ ነፃ የሆኑባቸውን ጊዜአት የነፃነት በዓል ብለው ሲያከብሩ እኛ ኢትዮጵያዊያን ግን የድል በዓላችንን እናከብራለን!'' ይህ የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሰራዊት በፋሺስቱ የጣሊያን ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ እና አስደማሚ ጥቃት በመሰንዘር የተገኘው መላው የሀገራችን አርበኛ ጀግኖች አባቶች እና እናቶች በወቅቱ የነበሩትን የሀገራችንን ንጉስ/መሪ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ንጉሰ ነገስት ዘ-ኢትዮጵያ እና ንግስት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ቀዳማዊት እመቤትን ፤ በተጨማሪም በወቅቱ የነበሩ በተዋረድ ያሉ ከመላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተዋጡ አመራሮችን ትዕዛዝ እና አመራር በአግባቡ በመቀበል በአንድነት የተገኘ አኩሪ በዓል ነው። ለዚህ ታላቅ የድል እና የኩራት ቀን የደረስነው ጀግኖች አርበኛ አባት እና እናቶቻችን የነፃነት አየር እንድንተነፍስ ፤ የእያንዳንዳችን ባህል ፤ ቋንቋ እና ትውፊት ተጠብቆ ይኖር ዘንድ ፤ ሀገራችንም እንደ ሀገር ነፃነቷ እና ክብሯ ተጠብቆ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ፤ ደማቸውን በማፍሰስ ፤ አጥንታቸውን በመከስከስ ፤ አንድያ ነብሳቸውን ያለ ስስት ለእኛ በመሰዋት ነውና በእጅጉ ትልቅ ዋጋ ሰጥተን ልናከብረው እና ልናወሳው ይገባል። ሌላው ለድሉ መንስኤ የሆነው ለሀገራችን የደህንነት ስጋት የነበረው የጣሊያን ጦር በትዕቢት መጥቶ ሀገራችንን በጉልበት ካልገዛሁ ማለት ሲሆን ለድሉ መገኘት ደግሞ የመላው የሀገራችን ህዝቦች በኢትዮጵያዊ ስነምግባር የፈጠሩት አንድነት እና መተባበር ነው!! ስለዚህ እኛ የዚህ ትውድ አባላት በአሁኑ ወቅት አዲስ ፤ የተለየ እና ነገ የሚያኮራ ታሪክ ለመስራት ከመነሳሳት ይልቅ #እኔ በሚል ክፉ አባዜ ተጠምደን ፤ እኔ ምን አገባኝ በሚሉ እና በሌሎች ታሪካችንን በማይመጥኑ ክፉ አሳቦች እና ተግባሮች ሀገራችንን የአንድነት አደጋ ላይ የጣልንበት ሁኔታ መሆኑን በመረዳት ፤ መለስ ብለን አስበን በሀይማኖት እና በዘር ሳንከፋፈል ስርዓት ባለው መንገድ ልክ እንደ ቀድሞአችን በመነጋገር ፤ በመከባበር ፤ አድንነታችንን በመመለስ ለቀጣይ ትውልድ የተለየ ታሪክ ባንሰጠው ሀገሪቷን ሳንሸራርፋት ማስተላለፍ እንዳለብን እንደ አንድ የሀገሪቱ ዜጋ ማሰሰብ እወዳለሁ!!! ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!! #127ኛው_የዓድዋ_ድል_መታሰቢያ! Photo Credit:-F.D.R.E Ministry Of Defense Facebook Page and Wikipedia TW® (at Addis Ababa, Ethiopia) https://www.instagram.com/p/CpRptTvo203/?igshid=NGJjMDIxMWI=














