ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት በነዋሪዎች ላይ የፈጸመው ግድያ በየአቅጣጫው ቁጣን ቀስቅሷል። የኮማንድ ፖስቱ ድርጊቱ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ቢገልፅም የመከላከያ ኃይሉ ጥቃት ሆን ተብሎ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት እንደኾነ የገለጡ አሉ።
{2}

Product Placement
PUT YOUR BEARD IN MY MOUTH
Color Me Curious
official daine visual archive
No title available
Cookie Run:Kingdom Official!
Sade Olutola

if i look back, i am lost
EXPECTATIONS
No title available

Origami Around
KIROKAZE
Mike Driver
No title available
macklin celebrini has autism
Aqua Utopia|海の底で記憶を紡ぐ
Interview Vampire Daily
art blog(derogatory)
Game of Thrones Daily

pixel skylines

seen from United States

seen from Türkiye
seen from Malaysia
seen from United States
seen from United Kingdom
seen from United States

seen from Ukraine
seen from United States

seen from United Kingdom

seen from Canada
seen from Malaysia
seen from Armenia

seen from Colombia
seen from United States

seen from Mali
seen from United States
seen from Malaysia

seen from Argentina
seen from Argentina
seen from Venezuela
@mantegaftotblog
ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት በነዋሪዎች ላይ የፈጸመው ግድያ በየአቅጣጫው ቁጣን ቀስቅሷል። የኮማንድ ፖስቱ ድርጊቱ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ቢገልፅም የመከላከያ ኃይሉ ጥቃት ሆን ተብሎ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት እንደኾነ የገለጡ አሉ።
{2}
Through my #office #window, a glimpse when #nature is #painting itself. #rheinriver #bonn #germany
Done! This is from California state Assembly: "Presented at the 8th annual Silicon Valley African Film Festival in recognition of your outstanding achievement in using film as a vehicle for community engagement and education. Thank you for strengthening our culture with your passion and creativity." At closing ceremony with Silicon Valley African Film Festival Director, Chike C. Nwoffiah #Gerreta #Ethiopia በካሊፎርኒያ ስቴት ሕግ አውጭ ጉባኤ በወርቅ ቅብ ማኅተም የተሰጠ ልዪ ዕውቅና:: "ፊልምን እንደ አንዳች መሣሪያ በመጠቀም ማኅበረሰቡ እንዲወያይና እንዲማማር ለተቀዳጁት ድንቅ ስኬት ዕውቅና በ8ኛው ዓመታዊ የሲሊከን ቫሊ የአፍሪቃ ፊልም ፌስቲቫል የተሰጠ:: በፈጠራ ሥራዎና በጥልቅ ስሜትዎ ባሕላችንን ስላጎለበቱ እናመሠግናለን::" እኛም የሳን ሆዜ የሐበሻ ማኅበረሰብን ጨምሮ ድጋፋችሁ ላልተለየን በሙሉ ከልብ እናመሠግናለን:: በካሊፎርኒያ ስቴት ሕግ አውጭ ጉባኤ በወርቅ ቅብ ማኅተም የተሰጠ ልዪ ዕውቅና:: #california #SVAFF #filmmaking #directing #cinematography #gerreta #ethiopia (at San Jose, California)
#africanfilmmakers at #siliconvalley #svaff 2017 #sanjose #california #film #filmmaker #cinematography Silicon Valley African Film Festival
With my lovely younger sister Rahel at the historic Hoover theater in San Jose, California Silicon Valley African Film Festival #SVAFF #Gerreta #ethiopia #cinematography #film #filmmaking #filmdirector (at San Jose Municipal Rose Garden)
Silicon Valley African film festival opens officially in the historic Hoover theater. With Sam Liccardo, Mayer of San Jose. #Gerreta #Ethiopia #cinematography #film #filmmaking (at San Jose Municipal Rose Garden)
Festival opening's at the historic Hoover theater. Silicon Valley African film festival. San Jose, California #SVAFF #Gerreta #Ethiopia #cinematography #film (at San Jose Municipal Rose Garden)
🎬Semi-Finalist! 🏆International award winning #ethiopian shot film #Gerreta has been granted Semi-finalist status at Kyiv Film Festival (Ukraine). #film #directing #cinematography #filmmaking #ethiopia Thank you to all who support us!!! በተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተጎናፀፈውና የተሽለመው "ግርታ" የተሰኘው ኢትዮጵያዊ አጭር ፊልም አሁንም በዓለም ዙሪያ መመረጡ እንደቀጠለ ነው:: አሁን ደግሞ ዩክሬን መዲና ኪዬቭ ውስጥ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ፊልሞች ልቆ ለግማሽ ፍፃሜ ደርሷል:: በዚህ ፊልም የተሳተፋችሁና ድጋፋችሁ ያልተለየን ወዳጆች በመላ ከልብ እናመሰግናለን! ፈጣሪ ዉለታችሁን ይክፈል::
#sun #shadowhunters #nature #dancing #filmmaking #film #light (at Bonn, Germany)
#fespaco2017 #gerreta #Ethiopia Award cermony starts at Palais des Sports soon.
With #BurkinaFaso director and Brakina the local bear. #gerreta audiences feedback was great! #Ethiopia #fespaco2017
አደገኛ የጉንዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ
በአካላዊ አወቃቀሩ እና ፈጣን ሥርጭቱ ልዩ የሆነ የጉንዳን ሠራዊት ከኢትዮጵያ ተነስቶ ለዓለም ስጋት ሊሆን ይችላል የሚል ዘገባ ሰሞኑ በወጣ ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ተገልጧል። የጉንዳን ሠራዊቱ ከባሕር ዳር አንስቶ እስከ ደብረታቦር ድረስ በአፈር ቅጠሉ ይርመሰመሳል።
በሳይንሳዊ መጠሪያው ሌፒዚዮታ ካንሴንስ (Lepisiota canescens) ይሰኛል። በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክፍል ከባሕር ዳር አንስቶ እስከ ደብረታቦር ድረስ በአፈር ቅጠሉ ይርመሰመሳል። በአይነቱ፣ በብዛቱ እና በአካላዊ መዋቅሩ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሌሎች ዝርያዎች ለየት ያለ ብቻ ሳይሆን አደገኛም ነው ተብሎለታል።
ተመራማሪዎች ይኽ የጉንዳን ሠራዊት ከአንዱ ግዛት ወደ ሌላኛው የጉንዳኖች ግዛት ያለ እክል መሰራጨት በመቻሉ መጠነ-ሰፊ የጉንዳን ሠራዊት ግዛት (supercolony) ሲሉ ሰይመውታል። በአንዳች አጋጣሚ ጉንዳኑ ከኢትዮጵያ ውጪ መሻገር ከቻለ ዓለምን በፍጥነት የማዳረስ አቅሙ ጠንካራ እንደሆነ ተመራማሪዎች ስጋታቸውን ገልጠዋል።
ለወትሮው አንድ ጉንዳን ከግዛቱ አልፎ የሌላ ጉንዳን ግዛት ውስጥ መኖር አይችልም። ያ ግዛቱም በአራት ኪሎ ሜትሮች ግፋ ቢልም በአምስት የተወሰነ ነው።
መንገድ ስቶ ወይ ደግሞ ንፋስ አንገዋሎት የሌሎች ጉንዳኖች ግዛት የደረሰ ከልታዋ ጉንዳን ግዛቴ ብለው ከሚርመሰመሱ ጉንዳኖች መልካም ነገር አይጠብቀውም። ያለማወላወል በግዛቱ ነዋሪ ጉንዳኖች ይገደላል። መጠነ-ሰፊ የጉንዳን ሠራዊት ግዛት የሚል ስያሜ ያገኙት ጉንዳኖችን ግን ከግዛት ግዛት ለመንሸራሸር የሚያግዳቸው የለም።
«ጉንዳኖች ማኅበራዊ እንስሳት ናቸው። በቡድን በቡድን ነው የሚኖሩት። በአንዲት ንግሥት የሚመራ አንድ ቡድን እንደ ሁኔታው ከአራት ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን ጉንዳኖች ሲኖሩት የሚኖረውም በአንድ አካባቢ ነው። ሌላ የጉንዳን ሠራዊት ደግሞ በዛው መጠን ሌላ ቦታ ይኖራል።
አሁን ያገኘነው የጉንዳን አይነት የሚኖረው ከባሕርዳር ከተማ ወጣ ብሎ ከሚገኝ አንድ ቤተ-ክርስቲያን ደን ጀምሮ ደብረታቦር እስከሚባለው ከተማ ድረስ ነው። የጉንዳኖቹ ቡድኖች በአንድ እዝ ስር የሚመሩ መጠነ-ሰፊ የጉንዳን ሠራዊት ግዛት የመሰረቱ ናቸው። ይኽ በጉንዳን ብዙ አልተለመደም። በተለይ ደግሞ ይኼ እኛ የምናጠናው ሌፒዚዮታ ካንሴንስ የተባለው የጉንዳን ዝርያ በባሕሪው አደገኛ እና ወራሪ ነው።»
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር አለማየሁ ዋሴ ይኽ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ክፍል ተገኘ የተባለው የጉንዳን ዝርያ ብዝኃ ሕይወት ላይ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።
ዶክተር ማግደሌና ሶርገር ከዶክተር አለማየሁ ጋር በመሆን በአካባቢው ብዝኃ ሕይወት ላይ ዘርፈ-ብዙ ጥናት ከሚያከናውኑ አምስት ተመራማሪዎች መካከል አንዷ ናቸው። ዩናይትድ ስቴትስ ሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ቤተ-መዘክር ውስጥም ምርምር ያከናውናሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኙት ጉንዳኖች ሰዎች ላይ በቀጥታ ጉዳት የሚያደርሱ ባይሆኑም ለብዝኃ ሕይወት ግን ጠንቅ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።
«ለሰው ልጆች አደገኛ አይደሉም። ግን ችግሩ ጉንዳኖቹ በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ብዝኃ ሕይወት ላይ ጣጣ ማስከተላቸው ነው።
ለምሳሌ ጉንዳኖቹ ወደ ሚገኙባቸው አንድ ቤተ-ክርስቲያን ደን ስናቀና ያገኘነው የነዚህ ጉንዳኖችን ዝርያዎች ብቻ ነው። ሌላ የጉንዳን ዝርያ ፈጽሞ የለም ማለት ይቻላል። ያ የሆነው ደግሞ በነዚህ ጉንዳኖች የተነሳ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም በጣም አደገኛ እና ጠበኛ በመሆናቸው ሌሎች የጉንዳን ዝርያዎችን በቀላሉ አጥፍተዋቸዋል። ችግሩ ይኼ ነው። ወደ ሌላው የዓለም ክፍል መሠራጨት ከቻሉ ሌሎች ነባር የጉንዳን ዝርያዎችን ሊያጠፉ ይችላሉ።»
ስለ እነዚህ ጉንዳኖች ምንነት እና ግኝት ሰሞኑን በዓለም ዙሪያ ይፋ ቢደረግም፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኙት ግን ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት መሆኑን ዶክተር አለማየሁ ዋሴ ተናግረዋል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም ግኝቱ በቤተ-ሙከራ ምርምር እየተደረገበት መቆየቱንም አክለዋል።
ዶክተር ማግደሌና ሶርገር ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኙት አደገኛ ጉንዳኖች ዝርያ ከሌሎች የጉንዳን ዝርያዎች የሚለዩባቸውን ነጥቦች ያብራራሉ።
«ጉንዳኖችን በአጠቃላይ ስናጠና የምንመለከተው አንዱ ነገር አራት የአካል ክፍሎች ያላቸው መሆኑን ነው። ራስ አላቸው። ደረት እና የሆድ ክፍል አላቸው። በሆድ ክፍሉ እና በደረቱ መካከል አነስ ያለ ማገናኛ ጉበን አላቸው። ይህ ማገናኛ አካል ከጉንዳን ጉንዳን የተለያየ ነው። ከጉንዳን ውጪ ሌላ አይነት ነፍሳት እንዲህ አይነት አካላዊ መዋቅር የለውም። ኢትዮጵያ ያገኘነው የጉንዳን ዝርያ ደረት እና ሆድ ማገናኛ ክፍሉ አንድ ነው። የሌሎች ዝርያዎች ማገናኛ ሁለት ነው።»
የጉንዳን ዝርያዎች በአጠቃላይ አራት ግዙፍ ቤተሰብ እንዳላቸው የተናገሩት ዶክተር ማግደሌና ሶርገር ባሕር ዳር አካባቢ የተገኙት ጉንዳኖች ከግዙፍ ቤተሰቦቹ አንደኛው ውስጥ የሚመደቡ ናቸው ብለዋል። እነዚህ ጉንዳኖች ከሌሎቹ የጉንዳን አይነቶች የሚለዩትም ጠላታቸውን የሚያጠቁበት ከበስተኋላቸው የሾለ መንደፊያ የሌላቸው በመሆኑ ነው።
እንደ ዶክተር ማግደሌና ማብራሪያ ይልቁንስ ጉንዳኖቹ ከበስተኋላቸው አሲድ የሚረጩበት አነስተኛ አካል ያላቸው ናቸው። የሾለ መንደፊያ ግን የላቸውም። ሌሎች ጉንዳኖችን እየጨረሱ በፍጥነት የሚሰራጩት እነዚህ ጉንዳኖች እንዳይስፋፉ ለማድረግ ጥናት እየተከናወነ መሆኑንም ዶክተር ማግደሌና ሶርገር ተናግረዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
http://bit.ly/2h9pxVO
Waiting...
የኤርባስ ኩባንያ ተሸላሚው ኢትዮጵያዊ መሀንዲስ
ለሽልማት አዲስ አይደሉም። በተሰማሩበት የምህንድስና ዘርፍ በተደጋጋሚ ተሸላሚ ኾነዋል። ኢትዮጵያዊው መሀንዲስ ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ። የዕውቁ የጃዝ ሙዚቃ ጠበብት፣ የኢትዮ ጃዝ አባት፦ ሙላቱ አስታጥቄ ታናሽ ወንድም። ዘንድሮ ሲሸለሙ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ቀደም ሲል የዓመቱ ጥቁር መሐንዲስ በሚል በሚኖሩበት ዩናይትድ ስቴትስ ለሽልማት በቅተዋል። ኢትዮጵያዊው መሀንዲስ ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ በበረራ ሥነ-ቴክኒክ፣ በኅዋ እና በመከላከያ ነክ ቁሳቁሶች አገልግሎት በመላው ዓለም ቀዳሚው እና ግዙፉ ኩባንያ ኤርባስ ቡድን ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። የኤርባስ ቡድን ከዓለም የምሕንድስና ዲኖች ካውንስል ጋር በመተባበር ሴውል ደቡብ ኮሪያ ውስጥ የሰጣቸው ይኽ ሽልማት ከ17 ሃገራት የተውጣጡ 40 መሀንዲሶች የተሳተፉበት ነበር። በውድድሩ እስከ መጨረሻው የገፉ ብቸኛው ጥቁር ተወዳዳሪም ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ ነበሩ። ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ ዩናይትድ ስቴትስ ቦልቲሞር ሜሪላንድ በሚገኘው ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምሕንድስና ክፍል ተባባሪ ዲን ናቸው። በዚህ ዩኒቨርሲቲ ምህንድስና ያስተምራሉ። ማስተማር ብቻም አይደለም ለየት ያለ ነገር ሲመለከቱ ለሀገሬ ተማሪዎች ይጠቅማል በሚል ያገኙትን አዲስ ነገር ለኢትዮጵያውያን በፍጥነት ያቀብላሉ። በኤሌክትሪካል ምህንድስና ዘርፍ ኢትዮጵያ እና አፍሪቃ ውስጥ የሚያበረክቱት አስተዋጽዖም ለሽልማት አብቅቷቸዋል። ለሽልማት ስላበቃቸው ሥነ-ቴክኒክ እንዲህ ያብራራሉ። ይህ ለምህንድስና ተማሪዎች የተግባር ልምምድ ጠቃሚ የሆነ አነስተኛ ቁስ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2009 ዓ.ም. ተሠርቶ ሲወጣ «ሞባይል ስቱዲዮ ቦርድ» ይባል ነበር። በአሁኑ ወቅት አምስት ኩባንያዎች በትብብር አነስተኛ ቁሱን በማሻሻል «አናሎግ ዲስከቨሪ» የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። አነስተኛ የልምምድ ቁሱ ቤተ-ሙከራ ሳይኖር በየትኛውም ቦታ ልምምድ ለማድረግ ያስችላል። የዶክተር ያዕቆብ የሥራ ዕቅድ (project) በዋናነት ያተኮረው ለኤሌክትሪካል ምህንድስና የተግባር ልምምድ የሚጠቅም አነስተኛ ቁስ በዝቅተኛ ዋጋ፤ በፍጥነት እና በስፋት እንዲዳረስ ማስቻል ላይ ነው። ራሼል ሽሮይደር ዶክተር ያዕቆብን ከሸለሙት ሁለት ድርጅቶች የአንደኛው ማለትም የግዙፉ ኤርባስ እና ኤርባስ ቡድን የሠራተኛ ቅጥር ገበያ ጥናት ኃላፊ ናቸው። ዶክተር ያዕቆብ በውድድሩ ወቅት ባቀረቡት ዝርዝር የሥራ ዕቅድ እና ትግበራ ከተወዳዳሪዎቹ ልቀው የተገኙትበትን ምክንያቶች ሲገልጡ «ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ ጎልተው የወጡት በአነስተኛ ወጪ በርካታ ነገር በመሥራታቸው ነው።» ብለዋል። ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄን የሸለመው የኤርባስ ኩባንያ ዓርማ ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄን የሸለመው የኤርባስ ኩባንያ ዓርማ «በእውነቱ በትንሽ ወጪ ኢትዮጵያ ውስጥ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አግኝተው እገዛ ሲያደርጉ መመልከት ይደንቃል። ያን ያደረጉትም በጣም ትንሽ በሆነ ወጪ ነው። እንደውም ለዚህ ውድድር የሥራ ዕቅዳቸውን ያስገቡ ሰዎች በአጠቃላይ ማለት ይቻላል የሳቸውን ተግባር ከልብ አድንቀዋል። በእውነቱ ለስብጥርነት ጽንሰ-ሐሳብ ከልብ ነው የሠሩት። በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪቃ የሚገኙ መሀንዲሶችን አቅም በመገንባትም ድጋፍ አድርገዋል» ሲሉም አክለዋል። ከመላው ዓለም የተውጣጡ መሀንዲሶች በተሳተፉበት የኤርባስ ቡድን እና የዓለም አቀፉ የምህንድስና ዲኖች ምክር ቤት ውድድር ከዶክተር ያዕቆብ ጋር ለፍጻሜ ከቀረቡት ሁለት ሰዎች አንደኛዋ ከታላቋ ብሪታንያ ናቸው። ሌላኛዋ ደግሞ ካናዳን ወክለው ነው የቀረቡት። አፍሪቃን ወክለው ከቀረቡ ተወዳዳሪዎች መካከል ከዶክተር ያዕቆብ በተጨማሪ አንዲት ደቡብ አፍሪቃዊት ቢገኙበትም ወደ ፍጻሜው ግን መምጣት አልቻሉም። በአጠቃላይ ከቺሌ፣ ከፈረንሣይ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከሌሎችም ሃገራት በርካታ ሰዎች የተሳተፉበት ውድድር ነበር። በውድድሩ ከ17 ሃገራት የተውጣጡ 40 ምሁራን የሥራ ዕቅዳቸውን አቅርበዋል። ሁሉም ተወዳዳሪዎች ሥራዎቻቸውን በዓለም አቀፍ የመሀንዲሶች ጉባኤ ላይ በአካል አቅርበው እንዲያብራሩ ሴውል ደቡብ ኮሪያ ተጋብዘዋል። ሥራዎቻቸውን ያቀረቡትም በዓለም አቀፍ ዳኞች ፊት ነው። በጽሑፍ ያቀረቡት የሥራ ዕቅድ ምን እንደሆነ፣ ከዚህ ቀደም ምን እንደሠሩ፣ የሥራ ዕቅዱ ምን ተጽዕኖ እንደሚፈጥር በመረጃ አስደግፈው ለዳኞቹ አቅርበዋል። ዶክተር ያዕቆብን አስታጥቄ አሁን ለሽልማት መብቃታቸውና ሀገራቸውን ማስጠራታቸው ብቻውን በቂያቸው አይደለም። ዘንድሮ ለሽልማት በበቁበት ዘርፍ በሚቀጥለው ዓመትም መሳተፍ ይፈልጋሉ። እስከዚያው ድረስ በዓለም መድረክ አወድሰዋቸው የሸለሟቸው ኤርባሶችም የምህንድስና ማዕከላትም የዶክተሩን ሥራ እየተከታተሉ እስከሚቀጥለው ዓመት ይዘልቃሉ። «ሽልማቱን የጀመረው ኤርባስ ሲሆን፤ የበለጠ እንዲዳብርም ከዓለም አቀፉ የምህንድስና ዲኖች ምክር ቤት ጋር ተገናኘ። ያን ያደረገውም በሁሉም አይነት የምሕንድስና ትምህርት ዘርፎች ስብጥርን ለማጎልበት እንዲቻል በተግባር አንዳች ነገር የሠሩ ሰዎችን ዕውቅና ለመስጠት በሚል ነው። የሽልማቱ ዋነኛ ዓላማም ብዙ ሰወች በምህንድስና እንዲማሩ እና በምህንድስና ዲግሪ እንዲመረቁ ማስቻል ነው። ትምህርቱም ልዩ ችሎታ ያላቸውን የበለጠ በማበረታታት የተሰባጠረ ልዩ ተሰጥዕ እንዲዳብር ማስቻል አለበት።» የኤርባስ ቡድን ባልደረባዋ ስብጥር ሲባል የጾታ፣ የዘር፣ የባሕል ብሎም የአስተሳሰብ በአጠቃላይ ሁሉንም አይነት ስብጥርነት የሚያካትት ሰፋ ያለ ትርጓሜ ያለው ነው ብለዋል። ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ ኢትዮጵያ ውስጥ በመመላለስ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላፕቶፖችን እንዲሁም ሌሎች የትምህርት አጋዥ ቁሳቁሶችን በመስጠትም ድጋፍ አድርገዋል። በተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት በመጓዝም ለምህንድስና ትምህርት መቀላጠፍ አስተዋጽዖ አበርክተዋል። በውድድሩ አሸናፊ በመሆናቸውም ዶክተር አስታጥቄ የ10 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆነዋል። ከምንም በላይ ግን በሽልማቱ ለአሸናፊዎች ዕውቅና መስጠት የውድድሩ ዓላማ እንደነበር የኤርባስ አውሮፕላን ኩባንያ ተወካዩዋ ገልጠዋል። «እነዚህ ሰዎች ማድረግ ያለባቸውን ቀድሞውኑ አድርገዋል። ግን ለእነሱ ዕውቅና መስጠቱ ጠቀሜታው በሌሎች ዘንድ በደንብ እንዲታወቁ ማድረጉ ላይ ነው። ሥራቸው በሌሎች ዘንድ ታይቶ ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ ሌሎች በተመሳሳይ እንዲሠሩት ለማድረግ በሚል ነው የተሸለሙት። ለውድድሩ ፍጻሜ የደረሱት ተወዳዳሪዎች በሠሩት ሌሎች እንዲማሩበት፤ ሁሉንም ባይሆን እንኳን በከፊል መልሰው እንዲሠሩት ለማድረግም ታስቦ ነው መሸለሙ ያስፈለገው።» ኢትዮጵያዊው መሀንዲስ ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ ቀደም ሲልም እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም. በማስተማር ልቀው ለወጡ መምህራን የሚሰጠውን የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ ሽልማት አግኝተዋል። ዘንድሮ በመላው ዓለም በብዛት ነጮች እና ወንዶች በሚሳተፉበት የምህንድስና ዘርፍ ከሁለት አውሮጳውያት ሴቶች ጋር ለፍጻሜ ቀርበው ለድል በቅተዋል። ለከርሞ ምን እንደሚሆን አይታወቅም። ምናልባትም ታላቅ ወንድማቸው፥ የጃዝ አባቱ ሙላቱ አስታጥቄ በሙዚቃ ቅንብሩ «የከርሞ ሰው» እንዳለው የከርሞን ለማየት እኛም «የከርሞ ሰው ይበለን» እንላለን። ማንተጋፍቶት ስለሺ © 2016 Deutsche Welle
Keep going...
ውቅያኖስ በድንኳ ፕላኔት፥ፕሉቶ
ምድር ከፀሐይ ከምትርቀው 40 ጊዜ እጥፍ ትርቃለች፤ ድንኳ ፕላኔት ፕሉቶ። ይኽች ከፕላኔቶች ወዲያ በርቀት የምትገኘው ድንክ ፕላኔት፥ ለዘመናት እንቆቅልሽ ሆና ቆይታለች። ከእነ አምስት ጨረቆቿ ከሥርዓተ-ፀሐይ ሽክርክሪት ጠርዝ ላይ ተንሳፋ ምሥጢር ሆና ዘመን ፈጅታለች። ካለፉት ስድስት ወራት አንስቶ ግን ፕሉቶ በየጊዜው አስደናቂነቷ እየጎላ ነው።
የበረዶ ቅይጥ የውቅያኖስ ውኃ ተገኝቶባታል
የድንኳ ፕላኔት ፕሉቶ ከርሠ ምድር ለሕይወት አመቺ በሆነ የበረዶ ቅይጥ የውቅያኖስ ውኃ የተሞላ መሆኑን የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ያመለክታሉ። አዲስ አድማስ (New horizons) የተሰኘችው ኅዋ ቃኝ መንኲራኲር እፕሉቶ ጥግ ደርሳ ድንኪቱን ፕላኔት ትበረብር ይዛለች። በበረዶ ግግር በተሞላው ከርሰ ምድሯ ፕሉቶ ከምድር የማይተናነስ የበረዶ ቅይጥ የውቅያኖስ ውኃ ሸሽጋ ኖራለች። ቋጥኞች፣ የበረዶ ግግሮች፤ አሁን ደግሞ የበረዶ ቅይጥ ውኃዋ ተደርሶባታል። ድንኳ ፕላኔት ፕሉቶ። እንደ ሥነ-ፈለክ እና ጠፈር ተመራማሪዎች ከሆነ ፕሉቶ ከፀሐይ 5.9 ቢሊዮን ኪሎ ሜትር ትርቃለች። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ1930 ዓመት መገኘቷ ይፋ ከተደረገ ወዲህ መጠኗ ብዙ ሲያጨቃጭቅ ቆይቷል። ፕሉቶ ፕላኔት ናት አለያስ ድንክ ፕላኔት ሲሉም ሳይንቲስቱ ሞግተዋል። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2006 ዓለም አቀፉ ሥነ-ፈለክ ኅብረት (IAU) ፕሉቶን ድንክ ፕላኔት ብሎ ሲሰይም ሦስት መስፈርቶችን በመዘርዘር ነበር።
ሦስት መስፈርቶች ታይተው ድንክ ፕላኔት ተብላ ተሰይማለች
በደቡብ አፍሪቃ፤ ኖርዝ ዌስት ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪው ዶክተር ጌትነት «አንደኛው መስፈርት ፕላኔቷ በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከር አለባት፣ ሁለተኛ የራሷ የሆነ ጠንከር ያለ ስበት ያስፈልጋታል፤ ሦስተኛበዙሪያው በቅርብ የሚሽከረከሩ ነገሮች መኖር የለባቸውት» ሲሉ ሦስቱን መስፈርቶችን አብራርተዋል። ሁለቱን መስፈርቶች የምታሟላው ፕሉቶ ሦስተኛውን መስፈርት ስለማታሟላ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2006 ሳይንቲስቱ ፕሉቶ፦ «ፕላኔት መሆኗ ቀርቶ ድንክ ፕላኔት መሆን አለባት ብለው ወሰኑ» ሲሉም አክለዋል። ዶክተር ጌትነት እርስ በእርስ የሚሽከረከሩ ጥንድ ከዋክብት (binary stars) የሽክርክሪት ባሕሪያትን በመቃኘት ጥልቅ ጥናት አከናውነዋል። ፕሉቱ አነስተኛ ከመኾኗ የተነሳ ከፕላኔት ጁፒተር 67 ጨረቆች መካከል ከአንደኛው ትልቁ ጨረቃ እንኳ በመጠን እንደምታንስ ተናግረዋል።
ውቅያኖስ በድንኳ ፕላኔት፥ፕሉቶ
ምድር ከፀሐይ ከምትርቀው 40 ጊዜ እጥፍ ትርቃለች፤ ድንኳ ፕላኔት ፕሉቶ። ይኽች ከፕላኔቶች ወዲያ በርቀት የምትገኘው ድንክ ፕላኔት፥ ለዘመናት እንቆቅልሽ ሆና ቆይታለች። ከእነ አምስት ጨረቆቿ ከሥርዓተ-ፀሐይ ሽክርክሪት ጠርዝ ላይ ተንሳፋ ምሥጢር ሆና ዘመን ፈጅታለች። ካለፉት ስድስት ወራት አንስቶ ግን ፕሉቶ በየጊዜው አስደናቂነቷ እየጎላ ነው።
የበረዶ ቅይጥ የውቅያኖስ ውኃ ተገኝቶባታል
የድንኳ ፕላኔት ፕሉቶ ከርሠ ምድር ለሕይወት አመቺ በሆነ የበረዶ ቅይጥ የውቅያኖስ ውኃ የተሞላ መሆኑን የቅርብ ጊዜ መረጃዎች ያመለክታሉ። አዲስ አድማስ (New horizons) የተሰኘችው ኅዋ ቃኝ መንኲራኲር እፕሉቶ ጥግ ደርሳ ድንኪቱን ፕላኔት ትበረብር ይዛለች። በበረዶ ግግር በተሞላው ከርሰ ምድሯ ፕሉቶ ከምድር የማይተናነስ የበረዶ ቅይጥ የውቅያኖስ ውኃ ሸሽጋ ኖራለች። ቋጥኞች፣ የበረዶ ግግሮች፤ አሁን ደግሞ የበረዶ ቅይጥ ውኃዋ ተደርሶባታል። ድንኳ ፕላኔት ፕሉቶ። እንደ ሥነ-ፈለክ እና ጠፈር ተመራማሪዎች ከሆነ ፕሉቶ ከፀሐይ 5.9 ቢሊዮን ኪሎ ሜትር ትርቃለች። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ1930 ዓመት መገኘቷ ይፋ ከተደረገ ወዲህ መጠኗ ብዙ ሲያጨቃጭቅ ቆይቷል። ፕሉቶ ፕላኔት ናት አለያስ ድንክ ፕላኔት ሲሉም ሳይንቲስቱ ሞግተዋል። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2006 ዓለም አቀፉ ሥነ-ፈለክ ኅብረት (IAU) ፕሉቶን ድንክ ፕላኔት ብሎ ሲሰይም ሦስት መስፈርቶችን በመዘርዘር ነበር።
ሦስት መስፈርቶች ታይተው ድንክ ፕላኔት ተብላ ተሰይማለች
በደቡብ አፍሪቃ፤ ኖርዝ ዌስት ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪው ዶክተር ጌትነት «አንደኛው መስፈርት ፕላኔቷ በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከር አለባት፣ ሁለተኛ የራሷ የሆነ ጠንከር ያለ ስበት ያስፈልጋታል፤ ሦስተኛበዙሪያው በቅርብ የሚሽከረከሩ ነገሮች መኖር የለባቸውት» ሲሉ ሦስቱን መስፈርቶችን አብራርተዋል። ሁለቱን መስፈርቶች የምታሟላው ፕሉቶ ሦስተኛውን መስፈርት ስለማታሟላ እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2006 ሳይንቲስቱ ፕሉቶ፦ «ፕላኔት መሆኗ ቀርቶ ድንክ ፕላኔት መሆን አለባት ብለው ወሰኑ» ሲሉም አክለዋል። ዶክተር ጌትነት እርስ በእርስ የሚሽከረከሩ ጥንድ ከዋክብት (binary stars)የሽክርክሪት ባሕሪያትን በመቃኘት ጥልቅ ጥናት አከናውነዋል። ፕሉቱ አነስተኛ ከመኾኗ የተነሳ ከፕላኔት ጁፒተር 67 ጨረቆች መካከል ከአንደኛው ትልቁ ጨረቃ እንኳ በመጠን እንደምታንስ ተናግረዋል።
አዲስ አድማስ ኅዋ ቃኝ መንኲራኲር
አዲስ አድማስ የተሰኘችው ኅዋ ቃኝ መንኲራኲር ተጠግታ እንደለካችው ከሆነ የፕሉቶ ገሚሰ-ክበብ አውታር (diameter) 2370 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። ምናልባትም ከኢትዮጵያ ሰሜናዊ ጫፍ እስከ ናይሮቢ ያለውን ርቀት የሚሸፍን ቢሆን ነው። ይኽ ርቀት ከምድር አንጻር ሲሰላ 18.5% እንደሚደርስ የዩናይትድስ ስቴትሱ ብሔራዊ የበረራ ሳይንስ እና የኅዋ አስተዳደር (NASA) አስታውቋል። እንደው በጥቅሉ ፕሉቶ የጨረቃን ሲሦ ብታህል ነው ማለቱ ይቀላል።
አዲስ አድማስ የተሰኘችው ኅዋ ቃኚ መንኲራኲር እዚህች ድንክ ፕላኔት ምኅዋር ውስጥ ገብታ ለመቃኘት ለዐሥር ዓመት ግድም ከንፋለች። «ኒውሆራይዘን መንኲራኲር የናሳ ሳተላይት ናት ወደ ኅዋም የመጠቀችው እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ006 ነው» ያሉት ዶ/ር ያብባል ታደሠ መንኲራኲሯ ፕሉቶ ጋር «ለመድረስ ረዥም ጊዜ ነው የፈጀባት» ብለዋል። «ፕሉቶ ጋር ከመጠጋቷ በፊትም ጁፒተር የተሰኘችው ፕላኔት ጋር ተጠግታ በርካታ ዳሠሣዎችን በማከናወን እስከዛሬ የማናውቀውን አዲስ ምስል ልካለች» ሲሉ አክለዋል።
ዶ/ር ያብባል ታደሠ ያልታሰሰውን የኅዋ ክፍል ለማጥናት በሚገነባው በዓለም ትልቁ የሬዲዮ ቴልስኮፕ ላይ ጥናት ለማከናወንም ደቡብ አፍሪቃ ይገኛሉ። በአውሮጳ የኅዋ ተቋም የጠፈር አፈጣጠር ምሥጢርን ለመፍታት አሠሣ በሚያደርገው የፕላንክ ሳተላይት የሚሰበሰቡ መረጃዎችን የሚተነትኑ ሣይንቲስትም ናቸው። ወደ ፕሉቶ ከዓመታት በፊት የተላከችው መንኲራኲር ፕላኔቶችን እና የኅዋ አካላትን ማጥኛ በርካታ መሣሪያዎች በውስጧ እንደተገጠሙላት ዶ/ር ያብባል ተናግረዋል።
ፕሉቶ ላይ የታየው ልብ ቅርጽ አንደምታው
መንኲራኲሯ በነዚህ መሣሪያዎቿ ባነሳችው ምስሎች እና መረጃዎች በመታገዝም ሳይንቲስቱ ስለፕሉቶ ምንነት ጥልቅ ግንዛቤ እያገኙ መኾናቸውን አስታውቀዋል። በተለይ ፕሉቶ ላይ የታየው የልብ ቅርጽ እና ቻሮን የተሰኘችው የፕሉቶ ጨረቃ ጉዞ አቅጣጫ ጥምረት ተመራማሪዎችን ድንኪቱ ፕላኔት በረዶ ቅይጥ ውኃ አላት የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ አስችሏል። «ቻሮን ከፕሉቶ ጨረቆች ትልቋ ናት» ያሉት ዶክተር ያብባል የዚህች ጨረቃ እና «ፕሉቶ ላይ የተገኘው የልብ ቅርጽ አቅጣጫ የተጣመረ አለያም የተንሰላሰለ በመሆኑ ፕሉቶ ውስጥ በረዶ ቅይጥ ውኃ ለመኖሩ ማስረጃ» እንደሆነ አብራርተዋል። ዶክተር ያብባል የጨረቃዋ እና የፕሉቶ ቅርፅ አቅጣጫ መመሳሰል «ሞገድ አለያም ስበት ለመኖሩ ጠቋሚ ነው» ብለዋል።
ፕሉቶን የሚዞሯት አምስት ጨረቆች ናቸው። ኬርቤሮስ፣ ቻሮን፣ ሃይድራ፣ ኒክስ እና ስቲክስ። በእነዚህ አምስት ጨረቆች ታጅባ ከሥርዓተ-ፀሐይ ጠርዝ ላይ የምትገኘው ትንሺቱ ፕሉቶ ቅዝቃዜዋ ወደር አይኝለትም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ዶ/ር ጌትነት ሲያብራሩ «አንድ ፕላኔት አለያም ድንክ ፕላኔት ከፀሐይ እየራቀ በሄደ ቁጥር እየቀዘቀዘ ነው የሚሄደው» ብለዋል። «ከጁፒተር ጀምረን፣ ሣተርን፣ ኡራነስ፣ ኔፕቲውን፣ ፕሉቶ እያልን ስንሄድ ቅዝቃዜያቸው በዛው እየጨመረ ነው የሚሄደው። ያ ማለት ወደ በረዶ የመቀየርም ባሕሪ አለው ማለት ነው።»
በበረዶ ግግር የተዋጠች ድንክ ፕላኔት
በእርግጥም ከፀሐይ በርቀት የምትገነው ፕሉቶ የተዋቀረችው በበረዶ ግግር ነው ሲሉ ሳይንቲስቱ ይናገራሉ። «የበረዶ እና የውኃ ቅልቅል አለ ነው የተባለው። አንዳንዶች የከርሠ-ምድር ውኃ ሲሉ ይጠሩታል። በብዛት አይታይም። ከላይ ያለው የፕሉቶ አካል በረዶ የሠራ አካል ነው» ሲሉ ትንታኔ የሰጡት ዶ?ር ጌትነት «ናይትሮጂን፣ ሚቴን እና ካርበን ሞኖክሳይድ ጋዞች ራሳቸው ፕሉቶ ላይ በበረዶ መልክ ነው ያሉት» ብለዋል። «የውኃው ክፍል ያለው ከነዚህ የበረዶ ግግሮች ስር ከ100 እስከ እስከ200 ኪሎ ሜትር ጥለቀት ላይ ነው የሚገኘው። ውኃው ክፍል ራሱ ወደታች 100 ኪሎ ሜትር ጥልቀት አለው።»
ድንኪቱ ፕላኔት ፕሉቶን ለማጥናት የተላከችው የናሳ መንኲራኲር መጠነ-ሰፊ መረጃዎችን ወደ ምድር ልካለች። መንኲራኲሯ ያነሳቻቸውን የምስል ክምችቶች እና ግዙፍ መረጃዎ ወደ ምድር ለመላክ የ15 ወራት ጊዜያት ፈጅቶባታል። እናም ይኽን ተልዕኮዋን አጠናቃ ከሥርዓተ-ፀሐይ ውጪ በማቅናት ላይ ትገናለች። «ኒው ሆሪዞን ለሁለት ዓላማ ነው የተላከችው» በማለት ዶክተር ጌትነት ያብራራሉ። «አንደኛው ፕሉቶን ለማጥናት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ከፕሉቶ ቀጥሎ 1.6 ቢሊዮን ኪሎ ሜትር የራቀ ሌላ ኪዩፐር ቤልት (Kuiper Belt object) የሚባል ቁስ አለ። መንኲራኲሯ ወደዚያ እያቀናች ነው» ብለዋል።
አዲስ አድማስ የዓመታት ጉዞዋ አላበቃም
በፕሉቶ ላይ ጥናቷን የጨረሰችው ቃኚ መንኲራኲር የመጨረሻ ግቧን ስትፈጽም እንደሌሎቹ መንኲራኲሮች እንድትከስም አትደረግም። ይልቁንም ከዚህ ቀደም ጥናታቸውን አከናውነው ከሥርዓተ-ፀሐይ በመውጣት በጥልቊ ኅዋ ላይ እንደተለቀቁት የናሳ ሁለት ሳተላይቶች በራሷ ጊዜ እየተንሳፈፈች እንድትጓዝ ትደረጋለች። እዛ ከመሄዷ በፊት ግን አንድ የመጨረሻ ግብ ይቀራታል። «እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር 2019 ላይ ከፕሉቶ ቅርበት ላይ የምትገኝን ሚጢጢ ፕላኔት (asteroids) ታጠናለች» ብለዋል። ዶክተር ያብባል አክለው ሲገልጡም መንኲራኲሯ «ትሪሊዮን ወደ ሆኑ ቁሶች ወዳሉበት ኪዩፐር ቤልትም» እንደምታቀና ገልጠዋል።
አዲስ አድማስ (New horizons) መንኲራኲር ከሥርዓተ-ፀሐይ ውጪ ስትወጣ የፀሐይ ብርኃን በጣም ደካማ ስለሚሆን ያለኃይል በዘፈቀደ ነው የምትጓዘው። እስካሁን በፕሉቶ ምኅዋር ላይ ሆና የሰበሰበችው ግዙፍ መረጃ በሳይንቲስቱ እየተተነተነ ነው። ምናልባትም 6.5 ጌጋ ባይት መጠን ያላቸው መረጃዎቹ በፕሉቶ ሕይወት ያለው ነገር ስለመኖሩ ወይንም የነበረ ስለመሆኑ ፍንጭ ይሰጡ ይሆናል። አዲስ አድማስ ግን ለተጨማሪ መረጃ የዓመታት ጉዞዋን ቀጥላለች። ፍለጋው አያበቃም። ማንተጋፍቶት ስለሺ
በድምጽ ለመስማት፦ ይኽን ይጫኑ! ውቅያኖስ በድንኳ ፕላኔት