ወገኖች የእግዝያብሔር ቃል ግፉአንን መርዳት መልካም ነው ይላል። በተለይም ስለእምነታቸው የሚሰቃዩን የቤተ ክርስትያን ልጆችን በስቃያቸው ወቅት መድረስ ክርስትያናዊ አደራችንም ጭምር ነው። ይሄንን የምፅፍላችሁ ሰሞኑን በሀገራችን ኢትዮጵያ በደረሰው የክፋት ሀይሎች ድርጊት፡ አርባ ዓመትና ከዚያ በላይ ከኖሩበት ሀገራቸው መጤ እየተባሉ ቤትና ንብረታቸው በእሳት የተቃጠለባቸው ክርስትያን ወገኖቻችንን ባለን አቅም እንድንረዳ ለመማፀን ነው። በሻሸመኔ ማርያም ቤተክርስትያን አገልጋይ የሆኑ ቀሳውስት፤ ዲያቆናት እና ክርስትያን ወገኖች፤ ባጠቃላይ 21 አባወራዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቤታቸው ተቃጥሎ ማሪያም በቤተክርስትያን ተጠልለው ይገኛሉ። ቃጠሎው ቅፅበታዊና በድንገት የደረሰ በመሆኑ እነዚህ ወገኖች ቅያሪ ልብስ እንኳን ሳይዙ ነፍሳቸውን ብቻ ለማትረፍ ወደ ቤተክርስትያን ሸሽተዋል። የነሱ እጣ ያልደረሰባቸው ሌሎች ወገኖች ምግብ እንዳያቀብሏቸው በቄሮ የበቀል እርምጃ ይወሰድባቸዋል። በመሆኑም እነዚህ ወገኖች በአሁን ሰዓት በቤተ ክርስትያን መቃብር ቤቶች ውስጥ ያለምንም እርዳታ ተጠልለው ይገኛሉ። ስለሆነም በዚህ እርዛትና ስቃይ ውስጥ የሚገኙ ክርስትያናዊ ወንድምና እህቶቻችንን፤ አባቶች ካህናትን እንደርስላቸው ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃችኋለን። በሚከተለው በኩል የምትችሉትን መርዳት ትችላላችሁ። Onepupil.org or transfer via zele @ [email protected] #enjera #ethiopianflag #shashemene #rasteferian #kinghaileselassie #negus #silase #peaceforallofus (at Kentlands, Gaithersburg, Maryland) https://www.instagram.com/p/CCPmciOgaCO/?igshid=lb06wiom67fr